ሐምሌ 4/2018
በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በመጪው ሳምንት ረቡዕ ይጀመራል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሌሎችም በምክክሩ በታዛቢነት እንዲገኙ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
ለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርቱ መሰረት በምክክሩ የሚሳተፉ ታዛቢዎችን ለጉባኤው ዝግጁ የማድረጉ ስራ እንዴት እየሆነ ነው?
በተቀመጡ አለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት መሰል የምክክር ሂደቶችን የመታዘብ ስራ ምክክሩ ከመካሄዱ 45 ቀን በፊት ጀምሮ መጀመር እንዳለበት ከባለሙያዎች ሰምተናል።
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ማቅረብ ያለባቸው የታዛቢዎች ቁጥር ተወስኖ እንዲያቀርቡ ኮሚሽኑ ጥሪ ማስተላለፉና ተቋማቱም ታዛቢዎቹን እያዘጋጁ መሆኑን በኮሚሽኑ የተደራሽነት እና አጋርነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፍሬሰናይ ገበየሁ ጠቁመዋል።
የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት በነበረው አጀንዳ የማሰባሰብና የተሳታፊዎች ልየታ ሂደቶች በሁሉም መድረኮቹ ታዛቢዎችን አሰማርቶ ምክረ ሃሳቦችን የመቀበል ልምድ እንዳለው ባለሙያው አቶ ፍሬሰናይ ተናግረዋል።
Comments