በተመልካች ቁጥር ማነስና በሌሎችም ችግሮች እየተፈተኑ ያሉትን የኢትዮጵያን የቲያትር ቤቶች
TRACK

በተመልካች ቁጥር ማነስና በሌሎችም ችግሮች እየተፈተኑ ያሉትን የኢትዮጵያን የቲያትር ቤቶች

Avatar

በተመልካች ቁጥር ማነስና በሌሎችም ችግሮች እየተፈተኑ ያሉትን የኢትዮጵያን የቲያትር ቤቶች ከችግራቸው ለማውጣት መንግስት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡

ከገንዘብ እጥረት ፣ እስከ ግብአት እጥረት ቲያትር ቤቶቹ በበረታ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡
ረዘም ላሉ ዓመታት በትያትር ሙያ ላይ የሰሩት አርቲስት አፅናፉ መኩሪያ የቲያትር ቤቶች መዳከም ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ትልቁ ችግር ግን መንግስት ለኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትኩረት አለመስጠቱ ነው ይላሉ።
ስለ ቲያትር በቂ ዕውቀት የሌላቸው ሰዎች በትያትር ቤቶች አስተዳደር ውስጥ ሲሾሙ ይታያል፣ ይህም የቲያትር ዘርፉን እንደጎዳው ያስረዳሉ።
ሌለኛው የቲያትር ባለሙያ አርቲስት መርዕድ ነጋሽ ደግሞ በኪነ-ጥበቡ ላይ መንግስት የጣለው ታክስ ቀድሞውኑ እምብዛም ገቢ የሌለው የቲያትር ዕድገት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ይላል።
ከዚህም በተጨማሪ አንድ የቲያትር ደራሲ ከገቢው ላይ የ30 በመቶ ክፍያ ብቻ ነው የሚያገኘው የሚለው አርቲስት መርዕድ ይህም አዳዲስ የቲያትር ድርሰቶች ከመድረኩ እንዲጠፉ ምክንያት እንደሆነ ያስረዳል።
የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ማነስ፣ የቴክኖሎጂ መስፋፋት እና የውጪ ፊልሞች ተፅዕኖ ዘርፉን ካዳከሙት ምክንያቶች መካከል ናቸው ሲሉ ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።

Comments

Avatar