TRACK
በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ያለባቸውን የገበያ ትስስር ችግር እና የቢዝነስ መረጃ እጥረት ይፈታል የተባለ ዲጂታል መላ ስራ ላይ ዋለ
ሚያዝያ 22 2017
በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ያለባቸውን የገበያ ትስስር ችግር እና የቢዝነስ መረጃ እጥረት ይፈታል የተባለ ዲጂታል መላ ስራ ላይ ዋለ፡፡
ጥቃቅንና አነስተኛ አምራቾች እንዲሁም ከዚያም በታች በኢ-መደበኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም እርስ በርስ የሚገበያዩበት እና መረጃ የሚያገኙበት ዲጂታል መላ “ለራስ” ይሰኛል ተብሏል፡፡
ለተጠቀሱት የንግዱ ዘርፍ አካላት ምቹ እንዲሆን ሆኖ በአማርኛ ቋንቋ የተሰናዳው “ለራስ” የዲጂታል የቢዝነስ ማቀላጠፊያ መላ በ”አፍሮ ቴንደር” ለምቶ ትናንት በይፋ ስራ ላይ ውሏል፡፡
በጥቃቅንና አነስተኛ አምራችነት የተሰማሩ እና በሌሎችም ዝቅተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሁሉ “Leras.Afrotender.com” ድረ ገፅ ላይ ተመዝግበው ጨረታዎችን በማየትና በመወዳደር፣ ምርቶቻቸውንም በማስተዋወቅ የቢዝነስ ስራቸውን ማበርታት ይችላሉ ተብሏል፡፡
Comments