‘’የገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጥሎብናል’’  የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር
TRACK

‘’የገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጥሎብናል’’ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር

Avatar

ሚያዝያ 16 2017

‘’የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በልኳንዳ ቤቶች ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጥሎብናል’’ ሲል የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ቅሬታውን አሰማ፡፡

አቤቱታውን ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በደብዳቤ ቢያሰማም ምላሽ እንዳላገኘ ማህበሩ ነግሮናል፡፡

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ምን አለ?

የሚጠበቅባቸውን #ግብር እየከፈሉ አይደለም በሚል አሁን እንድንከፍል የተደረገው የገቢ ግብር ከአቅማችን በላይ የሆነነ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ሳህሌ ነግረውናል፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት የቁም እንሰሳቱን ግዚን በተመለከተ ለቢሮው የምናቀርበው ደረሰኝ ተቀባይነት አይገኝም ይቀረባችሁት ደረሰኝ ህገወጥ ነው እንባላለን፤ የቁም እንሰሳት ነጋዴውን ሲስተሙ አያውቀውም እየተባለ እዳው ሁሉ እኛ ላይ እየተጫነብን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

Comments

Avatar