የንጹህ መጠጥ ውሃ ለማዳረስ ስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ የግል ተቋማት የፋይናንስ አቅርቦት ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡
TRACK

የንጹህ መጠጥ ውሃ ለማዳረስ ስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ የግል ተቋማት የፋይናንስ አቅርቦት ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡

Avatar

ሚያዝያ 16/2018

የንጹህ መጠጥ ውሃና ከንጽህና አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ስራዎችን በኢትዮጵያ ለማዳረስ ስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ የግል ተቋማት የፋይናንስ አቅርቦት ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡

የንጹህ መጠጥ ውሃና ንጽህና አጠባበቅ ወይም ሳኒቴሽን አገልግሎቶችን ማግኘት መብት ቢሆንም በኢትዮጵያ በብዙ ምክንያቶች ይህንን የሚያገኙት ካለው የህዝብ ቁጥር አኳያ ግን በቂ አይደሉም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በላይ በንጹህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎቱን በመደገፍ ሲሰራ የቆየው አኳ ፎር ኦል የተባለ አለምዓቀፍ ተቋም በዘርፉ የፋይናንስ ድጋፍ ከሚያቀርቡ ተቋማትና በግል በስራው ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር ባካሄደው ምክክር ላይ ነው ይህንን የሰማነው፡፡

በግል የንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ አገልግሎቱን ለመስጠት የፋይናንስ ምንጭ ማግኘት ዋነኛ ችግር በመሆኑ እዚህ ላይ እየሰራን ሲሉ የአኳ ፎር ኦል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ እዝቂኤል አይናለም ነግረውናል፡፡

Comments

Avatar