መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ዜጎች ወጪ አውጥተው ታክመውም እንዳይድኑ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ፡፡
TRACK

መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ዜጎች ወጪ አውጥተው ታክመውም እንዳይድኑ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ፡፡

Avatar

ሰኔ 8/2018

መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ዜጎች ወጪ አውጥተው ታክመውም እንዳይድኑ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ፡፡

የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በተገቢው እና በሀኪም ትዕዛዝ አለመወሰድ በሀገር ኢኮኖሚ ጉዳት እየደረሰ እና ዜጎችም ህይወታቸው እያጡ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህ ልማድ በተለይም የፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች ጀርሞች እንዲላመዷቸው ስለሚያደርግ፤ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ተነግራል፡፡

ይህንን ችግር ለመቀነስ ሰዎች የመድኃኒት አጠቃቀማቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ሲል የተናገረው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።

ይህ ችግር ከኢትዮጵያም በተጨማሪ በአለም ደረጃ ስጋት እየሆነ ነው ተብሏል፡፡

የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ (Antimicrobial Resistance / #AMR Day) የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በኢትዮጵያ ለ14ኛ ጊዜ ዛሬ ተከብሯል።

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጁት መድረክ ላይ ቀንኑ ስለ ጉዳዩ በሰፊው ተነስቷል፡፡

Comments

Avatar