የእግረ መንገድ ቱሪዝም ወይም (stop over tourism)
TRACK

የእግረ መንገድ ቱሪዝም ወይም (stop over tourism)

Avatar

ሚያዝያ 6/2018

የእግረ መንገድ ቱሪዝም ወይም (stop over tourism) በመባል የሚታወቀው የቱሪዝም አይነት ተጓዦች ከአንዱ ወደ ሌላው ሃገር ለመጓዝ መሸጋገሪያ በሚያደርጉት ሃገር እግረ መንገዳቸውን የሚያደርጉት ጉብኝት ነው።

ለዚህ ደግሞ በየአመቱ ብዙ ሚሊዮኖች ለአየር በረራው መሸጋገሪያ የሚያደርጓት አዲስ አበባ ተመራጭ እየሆነች ነው ተብሏል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእግረ መንገድ ቱሪዝም "የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝምን ለማሳደግ ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ባለፈው ዓመት ነበር የተፈራረሙት።

ከዚያስ በኋላ ምን እየተሰራ ነው ያልናቸው በዚህ ስራ ውስጥ በየደረጃው ካሉ የመንግስት ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ቢኒያም ታዬ ለተጓዦቹ ለ7 ቀናት የሚቆ ነፃ የቪዛ አገልግሎት ተጀምሯል፤ ለጉዞ የሚሆኑ የተለያዩ ፓኬጆችም ተዘጋጅተዋል ብለውናል።

Comments

Avatar