በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ።
TRACK

በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ።

Avatar

የመጋቢት 10/2018

በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ እና የህገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት የሚገታ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ።

በስራና ክህሎት ሚንስቴር እየተዘጋጀ ያለው ይህ ደንብ፣ በቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርሱ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል እንዲሁም የአሰሪዎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተነግረሯል።

ብዙ ጊዜ የቤት ሰራተኛ ሲባል ሰዉ የሚገነዘበዉ 70 በመቶ የሚሆኑትን ሴት የቤት ሰራተኞችን ብቻ ቢሆንም በዚህ ደንብ ግን አትክልተኛ፣ ሹፌሮችና ሌሎችም በመኖሪያ ቤት ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሰራተኛችን ጭምር እንደሚያካትት ተጠቁሟል።

በሚኒስቴሩ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ አዲሱ ደንብ በቀጣሪም በተቀጣሪም በኩል የሚነሱ ችግሮችና ፈተናዎችን የሚፈታ በተለያየ ጊዜ በሁለቱ መካከል ተደረጉ የሚባሉ አሰቃቂ ወንጀሎችንም ሚቀንስ እንደሆነ አስረድተዋል።

Comments

Avatar