ኢትዮጵያ  የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያ ማድረጓ ለኢትዮጵያ ባንኮችን ስኬት ወይስ እንቅፋት ሆናቸው?
TRACK

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያ ማድረጓ ለኢትዮጵያ ባንኮችን ስኬት ወይስ እንቅፋት ሆናቸው?

Avatar

ታህሳስ 24፣2017

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያ ካደረገች ስድስት ወር ሞላት፡፡

ያለፉት ስድስት ወራት ለኢትዮጵያ ባንኮችን ስኬት ወይስ እንቅፋት? የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው በባንኮች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምንድነው?

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንቲትዩት የባንክ እና ፋይናንስ ተመራማሪ የሆኑት የተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ጥናት ለእነዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል፡፡

ተወልደ ግርማ የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር እንዲሆን ሲወሰን ሁሌም ቢሆን በባንኮች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚሳድር ነግረውናል፡፡

በውጭ ገንዘብ ተበድረው የነበሩ ባንኮች ከማሻሽያው በፊት ይከፍሉት የነበረውን እዳ በሁለት እና በሶስት እጥፍ ከማሻሽያው በኋላ እንዲከፍሉ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ማሻሽያው በባንኮች የማይመለስ ብድር ላይም ከፍተኛ ጫና ማሳደሩንም ተመራማሪው በጥናታቸው ተመልክቻለው ይላሉ፡፡

በዚህም በውጭ ገንዘብ የተወሰዱ ብድሮች እስካሁን በሚፈለገው ደረጃ ለባንኮች እንዳልተመለሰም ዶ/ር ተወልደ ግርማ አስረድተዋል፡፡

Comments

Avatar