ጥቅምት 20፣2017
በሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ፕሮቲን እንዳለው ይነገራል፡፡
የሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ቅጠል በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል አካባቢ ለምግብነት ሲውል ይታያል፡፡
ተክሉ ከምግብነት ባለፈ ለመድሃኒትነትም ጥቅም እንዳለው ከዚህ በፊት በተደረጉ ጥናቶች የተረጋገጠ ሲሆን አሁን ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ባደረገው ምርምር ለመቀንጨር ችግር ፍቱን መሆኑን ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
ጥናቱን ያካሄደው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል በተለያየ መንገድ አዘጋጅቶ ህፃናትን መመገብ የመቀንጨር ችግር እንደሚፈታ በጥናት መረጋገጡን ዩንቨርስቲው አስረድቷል፡፡
ጥናቱን ያካሄዱት በዩኒቨርስቲው ተመራማሪ የሆኑት አዲሱ ፍቃዱ(ዶ/ር) እንዳሉን ሞሪንጋን ከተለያዩ ምግቦች ጋር አቀነባብረን መመገብ ከፍተኛ ፕሮቲን እንድናገኝ ይረዳል፡፡
Comments