አዩቴ አፍሪካ የውድድር መረሀ ግብር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊከናወን መሆኑም ተነግሯል
TRACK

አዩቴ አፍሪካ የውድድር መረሀ ግብር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊከናወን መሆኑም ተነግሯል

Avatar

ግንቦት 14 2017

ከ80 በመቶ በላይ ህዝብ ግብርናው ላይ መሰረት ባደረገ ኢኮኖሚ ኑሮውን ይገፋል፡፡

ታዲያ መተዳደሪያ የሆነው የግብርናው ዘርፍ አሁንም ድረስ ከባህላዊ አስተራረስ እና አመራረት ዘዴ መላቀቅ አልቻለም፡፡

ዘርፉ እንዲዘምንም የተለያዩ ተቋማት በየፊናቸው ስራዎችን ሲከውኑ ይታያል፡፡

ከእነዚያም መካከል ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተሰኘ ተቋም አንዱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍን መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተቋም አዩቴ አፍሪካ የተሰኘ የውድድር መረሀ ግብር ይከውናል፡፡

ለ3 ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን የሚያግዙ የፈጠራ ሀሳቦችን በማወዳደር ላይ ያተኮረው አዩቴ አፍሪካ የውድድር መረሀ ግብር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊከናወን መሆኑም ተነግሯል፡፡

ውድድሩም ትኩረት የሚያርገው የኢትዮጵያን ግብርና ሊያዘምን የሚችል ማንኛውም የፈጠራ ሀሳብ ያለው ጉዳይ ላይ ነው የተባለ ሲሆን በተለይ ሴት ተወዳዳሪዎችን የሚያበረታታ ነው ተብሎለታል፡፡

Comments

Avatar