00:00
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የሚገላበጠው አብዛኛው ገንዘብ ወይንም ከ73 በመቶ በላዩ የሚዟዟረው በዲጂታል መንገድ ነው፡
በተያዘው የበጀት አመት በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 14.56 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል መንገድ ተገላብጧል፡፡
ይህ በዲጂታል ገንዘብ ማስተላለፍ ጊዜን የሚቆጥብ ፣ ምቹ መሆኑ ቢጠቀስም የአገልግሎት ክፍያውና ሌሎች ተቆራጮች መኖርና ለአጭበርባሪዎች የተጋለጠ ነው በሚልም ይወቀሳል፡
መንግስታዊ ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያቸውን ወደ ድርጅት ባንኪንግ ማዞራቸውን ተከትሎ ከማህበረሰቡ ለአገልግሎት እየተባለ የሚቆረጠው ገንዘብ እየበዛ መጥቷል፡፡
ደሞዝተኛውም ይሁን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተለያዩ የክፍያ ስርዓቶች የሚያደርጉት የገንዘብ ልውውጥ ተደራራቢ ታክስ እንዲከፍሉ አያደርግም ? በጉዳዩ ላይ የዘርፉን ባለሙያዎች ጠይቀናል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments
00:00