መስከረም 23 2018
በነዳጅ ሀይል የሚሰሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ አይገቡም ተባለ።
በዚያ ምትክ በ #ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስገቡ የቀረጥ ነፃ እድል ይሰጣል ተብሏል።
ይህንን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ውስጥ በስራ ላይ ያሉ 2,000 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችም ከነዳጅ ተጠቃሚነት ወደ ጋዝ እንዲቀየሩ የማድረግ ስራ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይሰራል ብለዋል።
Comments