በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ አስፈትቶ መልሶ ማቋቋም ባለመቻሉ በትግራይ ግዙፍ የታጠቀ ሀይል መኖሩን አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል፡፡
TRACK

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ አስፈትቶ መልሶ ማቋቋም ባለመቻሉ በትግራይ ግዙፍ የታጠቀ ሀይል መኖሩን አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል፡፡

Avatar

መጋቢት 4 2017

በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመመካከር ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የክልሉ አስተዳደር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡

ክልሉ እየታመሰ እና ጊዜያዊ አስተዳደሩም እየተፈተነ ያለው በፖሊስ አካላት ብቻ ሥርዓት መያዝ በሚችሉ ችግሮች ነው ሲሉም ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡፡

በመሆኑም ክልሉ የፌዴራል መንግስቱ አካል እንደመሆኑ ክልሉ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ዳግም እንዳይገባ ሁሉንም አማራጮችና እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተር ትጥቅ አስፈትቶ መልሶ ማቋቋም ባለመቻሉ በትግራይ ግዙፍ የታጠቀ ሀይል መኖሩን አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል፡፡

Comments

Avatar