የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የፋይናንስ ተቋም ኪሳራ ላይ ሲወድቅ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚከፍለውን ኢንሹራንስ
TRACK

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የፋይናንስ ተቋም ኪሳራ ላይ ሲወድቅ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚከፍለውን ኢንሹራንስ

Avatar

ጥር 29/2018

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የፋይናንስ ተቋም ኪሳራ ላይ ሲወድቅ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚከፍለውን ኢንሹራንስ ከመቶ ሺህ ብር ከፍ ለማድረግ እያሰበበት እንደሚገኝ ተናገረ፡፡

አሁን ላይ ኪሳራ ለደረሰበት አንድ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ገንዘብ አስቀማጮች ኢንሹራንስ እየከፈልኩ እገኛለሁም ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ላስቀመጡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ፤ የኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለገንዘብ አስቀማጮች ጥበቃ ለማድረግ የተቋቋመ ነው።

ከተቋቋመ ወደ ሶስት ዓመት እየተጠጋ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ በአጠቃላይ ከአባል ፋይናንስ ተቋማት የሰበሰበው አረቦን 17 ነጥብ 80 ቢሊየን ብር መድረሱን ሠምተናል።

Comments

Avatar