ነሐሴ 3፣2016
የምግብ ዋስትና ችግር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ችግርን አክፍቶታል ተባለ፡፡
በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረው የሰላም እጦት አምራች የነበረውን ማህበረሰብ እንዳያመርት ስላደረገው የምግብ ዋስትናን እየፈተነው መሆኑን የግብርና ባለሙያው አቶ ሳለ ጌታሁን ይናገራሉ፡፡
ከሶስት አስርት አመታት በላይ በግብርናው ዘርፍ የሰሩት አቶ ሳለ ጌታሁን እንደሚሉት ከሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአፈር መሸርሸር መጨመር፣ ሀገሪቱ ያላትን የቀንድ ከብት ባግባቡ አለመጠቀሟ፣ ባህላዊ የግብርና አስተራረስ ዘዴን መጠቀማችን፣ ድርቅ እና ሌላ ሌላውም ችግር ሲታከልበት፣ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት የምግብ ዋስትና ማጣት ተዳርጋለች፡፡
Comments