በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ግጭት ምክንያት የተበዳዮችን ቅሬታ መሰብሰብ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ
TRACK

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ግጭት ምክንያት የተበዳዮችን ቅሬታ መሰብሰብ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

00:00

ሐምሌ 17፣ 2016

በhገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ግጭት ምክንያት የተበዳዮችን ቅሬታ መሰብሰብ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡

በዚህም ምክንያት በተጠናቀቀው ዓመት ካሰብኩት ውስጥ ያሳካሁት 53 በመቶውን ብቻ ነው ብሏል፡፡

የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮች ጉዳያቸውን ይዘው ወደ እምባ ጠባቂ ተቋም በማምራት አቤቱታቸውን ያሰማሉ፡፡

ተቋሙም በፍርድ ከተያዙ ጉዳዮች፣ የሃገርን ደህንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉና የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ውጭ ያሉ ሁሉንም አይነት ጉዳዮችን ተቀብሎ በመመርመር ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

Comments

00:00