00:00
ጥቅምት 14፣2017
ከወራት በፊት ከየመን ወደ ጅቡቲ የባህር ዳርቻ 320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በመያዝ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች በመስጠማቸው 48 ኢትዮጵያዊያን መሞታቸው ይታወሳል፡፡
በወቅቱ 197 ሰዎች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ ወደሚገኘው የአለም አቀፍ የስደተኞች ካምፕ እንዲገቡ መደረጉም ተነግሯል፡፡
መቀመጫውን በጅቡቲ ያደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትናንትናው እለት ከወር በፊት ከአደጋ ተርፈው ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ከገቡ ሰዎች መሀከል 37 ሰዎችን የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ከአለም አቀፉ የፍልሰት ተቋም(IOM) ጋር በመተባበር ወደ ሀገር መመለሱን ተናግሯል፡፡
ከየመን ወደ ጅቡቲ የባህር ዳርቻ የሚደረገው ጉዞ ህገ-ወጥና አደገኛ መሆኑን የተናገረው በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የቀሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር ለመመለስ ከሌሎች ተቋማት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡
Comments
00:00