ሰኔ 6 2017
የኦዲት ግኝቶችን መሠረት በማድረግ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ላይ በርካታ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ክፍተት ታይቶባቸዋል ተባለ።
ፍትህ ሚኒስቴር እንዳለው በመስሪያ ቤቶቹ ላይ ተደጋጋሚ የፋይናንስ አስተዳደር ጥሰቶች እየታዩ ሲሆን፤ ከግዥ ጋር የተያያዙ ችግሮችም አልተፈቱም።
የፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል ዋና ኦዲተርን የ2013 እና የ2014 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሪፖርት መነሻ በማድረግ፤ በ87 የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ላይ የዳሠሣ ጥናት አካሂዶ ውጤቱን አሳውቋል።
አብዛኞቹ መስሪያ ቤቶች የፌዴራል ዋና ኦዲተር ግኝቶችን እና የሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች በመቀበል ማስተካከያ ማድረግ ላይ ጉድለት እንዳለባቸው ጥናቱ አሳይቷል ተብሏል።
ጥናቱን ካካሄዱት ሞያተኞች አንዱ የሆኑት በፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል ህጎች ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግና፤
ቡድን መሪ አቶ ሃይለገብርኤል አያሌው እንደሚሉት ከዋና ኦዲተር ግኝት በኋላም በመስሪያ ቤቶቹ የፋይናንስ አስተዳደር ላይ ተደጋጋሚ ጥሰቶች ታይተዋል።
Comments