ሚያዝያ 16 2017
መሰረቱን በህንድ ያደረገው ቫይደም የተሰኘው የህክምና አማካሪ ተቋም በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፈትኩ አለ፡፡
እንደ ኩላሊት፣ የመቅኔ ንቅለ ተከላ እና ሌሎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚደረጉ ህክምናዎችን የማማካር እና የጉዞ ሂደትን ማመቻቸት ላይ ትኩረት አድርጌ እሰራለሁ ብሏል፡፡
ወደ ውጭ ሀገር ለህክምና ለመውጣት ሲታሰብ የት ሀገር፣ የትኛው ሆስፒታል ልታከም እና ሌሎችም ለታማሚውም ሆነ ለአስታማሚው ቤተሰብ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያለው የቫይደም ሄልዝ ሜዲካል ኮንሰልተንሲ ሰርቪስ በተለይ አጣዳፊ የህክምና ጉዞ ከሆነ ሊያጋጥማቸው የሚችለው ችግር ቀላል አይደለም ብሏል።
ለዚህ ደግሞ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ቢሮ መክፈቱ ጥቅሙ ቀላል የሚባል አይደለም የተባለ ሲሆን ታካሚው ትክክለኛ ሀኪም እና ሆስፒታል እንዲያገኝ ያግዛል ተብሏል።
Comments