ሐምሌ 24፣2016
በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መናድ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የ243 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል፡፡
13 የአካባቢው ሰዎች የት እንደገቡ ባይታወቅም ፍለጋው ግን መጠናቀቁ ተሰምቷል፡፡
10 ሰዎችን ደግሞ በነፍስ አድን ስራው በህወት ማትረፍ እንደተቻለም ተነግሮዋል፡፡
በትናትናው እለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ በመሬት ናዳው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስክሬን ፍለጋውም ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከክልሎች ጋር በመሆን እስከ 15,000 ለሚሆኑ ሰዎች በዘላቂነት ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ስራ እየከወንኩ ነው ብሏል፡፡
Comments