00:00
ነሐሴ 14፣2016
ከኢትዮጵያ ህዝብ ከኤሌክትሪክ ሀይል ጋር የተገናኘው 60 በመቶው እንደሆነ ይነገራል፡፡
ይህም ቢሆንም አብዛኛው በኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ የሚቸገር ሲሆን በአምፑል፣ በኬብል፣ በሶኬት ብልሽት የሚማረረውም ቁጥሩ የበረከተ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዎች፣ ማሰራጫ እና መስፋፊያ እቃዎች በአብዛኛው ከውጭ ሲገቡ ቆይተዋል፡፡
በአሁኑ ምን ያህሉን ፍላጎት ይሸፍናሉ ተብሎ ቢጠየቅ መልስ ባይገኝም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ግን አሉ፡፡
የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ አምፑሎች እና ሌላም የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ እቃዎች ጥራት ጉዳይ ግን እንዲህ በሰፊው የሚታየው ለምንድነው?
25 በኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ፣ ማሰራጫ እና ማከፋፈያ አምራችን የያዘው ማህበር በእቃቹ ላይ የጎላ የጥራት ችግር የሚያደጋገምበት ምክንያት ብዙ ነው ይላል፡፡
የማህበሩ ፕሬዘዳንት አቶ ወንድወሰን በላይ ደረጃቸው ያለጠበቁ የምርት ግብዓቶች፣ የቁጥጥር መላላት እንዲሁም ተጠቃሚው ስለምርቶቹ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆንን በዋና ምክንያትነት ያነሳሉ።
‘ኤዲሰን’ በሚል ምርት የኤሌክትሪክ እቃዎችን በማምረት 10 ዓመታት ያስቆጠረው ‘ዩኒማስ ኢንጂነሪግ’ በበኩሉ ‘’ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሀይል እቃዎች ማምረት በጣም ከባድ ነው’’ ብሏል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ መሃመድ ሙዘይን ‘’የኤሌክትሪክ እቃዎችን ለማምረት ከባለሞያ ጀምሮ እጥረት አለ፣ ገበያውም ምስቅልቅሉ የወጣ ነው’’ ብለዋል።
Comments
00:00