የናይል ተፋሰስ ሀገራት የግድብ ደህንነት ማዕከልን ለማቋቋም በሚያስችሉ ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡
TRACK

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የግድብ ደህንነት ማዕከልን ለማቋቋም በሚያስችሉ ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡

00:00

የካቲት 26 2017

#የናይል_ተፋሰስ_ሀገራት የግድብ ደህንነት ማዕከልን ለማቋቋም በሚያስችሉ ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡

በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው ምክክር ላይ የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎረንስ ግሬሶ መገኘታቸውንና ጠንካራ አካባቢያዊ የናይል የተፋሰስ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ መናገራቸውን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰምተናል፡፡

ባለፉት አመታት የተፋሰሱን የግድብ ደህንነት የስልጠና ማዕከል ለማቋቋም የተዳረጉ ጥረቶች በሀገሪቱ የውሃ ሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባዎች መቅረባቸው ውጤታማ መሆናቸው ሚኒስትር ሀብታሙ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የግድብ ደህንነት የስልጠና ማዕከልን ማቋቋም ለታችኞቹ ሀገራት ጭምር ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን እና በተለይም የአየር ጠባይ ለውጥ በሚከሰትበት ጊዜ ጠንካራ ትብብርን ለማድረግም ይረዳል ተብሏል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

Comments

00:00