የካቲት 28፣2016
በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ስራ አቆሞ የነበረው እና በትግራይ ክልል የሚገኘው የአሸጎዳ ነፋስ ሃይል ማመንጫ ከሶስት ዓመት በኋላ ዳግም ስራ መጀመሩ ተነገረ።
በትግራይ ክልል የሚገኘው አሸጎዳ የነፋስ ሃይል ማመንጫ ስራ የጀመረው 2006 ላይ ነበር።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ግን የነፋስ ሃይል ማመንጫው ለሶስት አመታት ስራ አቆሞ እንደቆየ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል።
በጦርነቱ ምክንያት ለሃይል ማመንጫው ተገቢውን ጥገና ማድረግ ባለመቻሉ ስራ አቁሞ ቆይቷል ብለዋል።
Comments