የእንቦጭ አረምን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ህዳሴ ግድቡ ጋር ሊሄድ ይችላል ሲል የብዝሃ ህይወት ኢኒስቲትዩት ተናገረ።
TRACK

የእንቦጭ አረምን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ህዳሴ ግድቡ ጋር ሊሄድ ይችላል ሲል የብዝሃ ህይወት ኢኒስቲትዩት ተናገረ።

Avatar

የካቲት 19፣2016

የጣናን ሐይቅ 24,000 ሄክታሩ የሸፈነው የእንቦጭ አረምን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ህዳሴ ግድቡ ጋር ሊሄድ ይችላል ሲል የብዝሃ ህይወት ኢኒስቲትዩት ተናገረ።

የመጤ አረሙ ሽፋንም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየጨመረና እየተስፋፋ እንደመጣ የተነገረ ሲሆን፤ ከጣና ሐይቅ ባለፈ ለቆቃ፣ ለባቱ እና ለሌሎች ሐይቆችም ስጋት መሆኑን ኢኒስቲትዩት እወቁት ብሏል።

በኢኒስቲትዩቱ የጄኔቲክ ሀብት አርክቦት እና ጥቅም ተጋሪነት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት መጤ አረሙ በአካባቢው እንዲሰፋፋ እና የመከላከል ስራው ችላ እንዲባል ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

መጤ አረሙን ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መከላከል ካልቻሉ ዛሬ ለልማት ተብለዉ እየተገነቡ ባሉ ግድቦች እና የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይም ጉዳት ማድረሱ አይቀርም ተብሏል።

ዓሳን ጨምሮ በባህር ውስጥ ያሉ ብዝሃ ሕይወቶችን ማጥፋት፣ የውሃ ክምችትን ከመቀነስ እስከ ማጥፋት፣ የእርሻ እና የግጦሽ መሬት መውረር መጤ አረሙ ከሚያደርሳቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል።

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ጣና_ሐይቅ #እንቦጭ #መጤ_አረም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar