የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በአማራ ክልል ደርሰዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጥቆማ አልደረሰኝም ሲል ተናግሯል
TRACK

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በአማራ ክልል ደርሰዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጥቆማ አልደረሰኝም ሲል ተናግሯል

00:00

የካቲት 11፣2016

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዋናነት በታወጀበት አማራ ክልል የተለያየ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሰዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡

የአዋጁን አፈጻጸም የመከታተል ሀላፊነት ተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በበኩሉ ደርሰዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጥቆማ አልደረሰኝም፤ የአዋጁ አፈፃፀምም መልካም በሚባል ደረጃ እየሄደ ነው ይላል፡፡

በቅርቡ በመራዊ ከተማ በንጹሃን ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ጥቃት በተመለከተም የሰማሁት ከመገናኛ ብዙሃን ነው፤ በስፍራው ተገኝቶ ለመመርመር የሚያስችለኝ ሁኔታ ከተመቻቸ ሁኔታውን ላጣራ እችላለሁ ሲል ለሸገር ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የአስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ #አማራ_ክልል #የሰብአዊ_መብት_ጥሰት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00