በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተበራክተዋል ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተናግሯል
TRACK

በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተበራክተዋል ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተናግሯል

Avatar

የካቲት 27፣2016

በለንደን የሚገኘዉ የኤርትራ ኤምባሲ ባለፈው ያወጣው መግለጫ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ክልል እንደሚገኝ ያረጋገጠ ነዉ ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተናግሯል።

በለንደን የኤርትራ ኤምባሲ፤ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት እንደሌሉ ተነግሮ አሁን የያዛቸው ቦታዎችም የኢትዮጵያ ሳይሆን ሕውሃት ከ20 ዓመት ባላይ በሃይል ይዞት የቆየው የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት መሆኑን አስረድቶ ነበር፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ፤ የኤምባሲው መግለጫ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ እንደሌለ ሳይሆን መኖሩን ያረጋገጠ ነዉ ሲል ተናግሯል።

በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ተበራክተዋል ሲሉ የነገሩን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ረዳይ ሃለፎም ናቸዉ።

ሃላፊው በኤርትራ ሰራዊት የተያዙ አካባቢዎች ማለትም የኩናማ እና የኢሮብ ማህበረሰብም የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል።

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የኤርትራ_ሰራዊት #ትግራይ_ክልል

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar