ነሐሴ 21፣2016
ሰሞኑን እየጣለው ባለው ዝናብ ከደቡብ ትግራይ እና ከስልጤ ዞን 10,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ፡፡
በስልጤ ዞን ከ 6,000 በላይ ሰዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ሳሊያ አብደላ ነግረውናል፡፡
በዞኑ አከታትሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ስምንት ቀበሌዎች በጎርፍ መጥለቅለቀዘቸውን ሃላፊው ነግረውናል፡፡
በዚህም በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ከባድ ጉዳት ባይኖርም ከ1,100 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የለማ የቦቆሎ፣ ስንዴ እና መሰል ሰብል ሙሉ በሙሉ ወድሟል ተብሏል፡፡
ዞኑ አሁን ካለው ችግር ይልቅ የሚመጣው ያሰጋኛል ሲል ተናግሯል፡፡
ከቄያቸው የተፈናቀሉትም በችግር ላይ እንዳሉ የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ሳሊያ አብደላ ነግረውናል፡፡
በደቡብ ትግራይ ዞን በተከሰተ የጎረፍ አደጋ 4,000 ሰዎች መፈኛቀላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የጣለው ዝናብ በሰብል እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ተነግሯል፡፡
ያረድ እንዳሻው
Comments