TRACK
በሸገር ከተማ አስተዳደር ከዚህ በኋላ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎችን ለመቅጣት መንጃ ፍቃድ መቀበል፣ የመኪኖችንም ታርጋ መፍታት አይኖርም ተባለ
ሚያዝያ 30 2017
በሸገር ከተማ አስተዳደር ከዚህ በኋላ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎችን ለመቅጣት መንጃ ፍቃድ መቀበል፣ የመኪኖችንም ታርጋ መፍታት አይኖርም ተባለ።
አሽከርካሪዎች ጥፋት ከፈጸሙበት ቦታ ሳይንቀሳቀሱ ቅጣታቸውን መክፈል የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ማዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል።
ስራ ላይ የዋለው አዲሱ ቴክኖሎጂ ሞያተኞች ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ያበለፀጉት እንደሆነ ሠምተናል።
ረጅም ጊዜ ከፈጀ ሙከራ እና ፍተሻ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ ስራ ላይ መዋል መጀመሩን የሸገር ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ያሲን አህመድ ነግረውናል።
Comments