በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ መቸገራቸውን ሸገር ሰምቷል
TRACK

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ መቸገራቸውን ሸገር ሰምቷል

00:00

ሐምሌ 1፣ 2016

በኢትዮጵያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እጥረት በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ችግሩ የሰፋ ነው ተባለ።

በሌላ በኩል ደግሞ የንፁህ ውሀ አቅርቦት ባለባቸው አካባቢዎች ብክነቶቸ እየታዩ መሆኑ ይነገራል፡፡

በተለይ በከተማ አካባቢ ችግሩ በስፋት እንደሚታይ ወተር ኤድ ኢትዮጵያ (Water Aid Ethiopia) ተናግሯል፡፡

በከተማ እና በገጠር አካባቢዎች ንፁህ ውሀ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ለረጅም ዓመታት ሲሰራ የቆየው ወተር ኤድ ኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች ባሉ የውሀ አገልግሎቶች ብክነቶችን አስተውያለሁ ብሏል።

የንፁህ ወሀ አቅርቦት ከማስፋት በዘለለ በአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ዙሪያ እየታየ ያለውን ችግሮች ለመቀነስ የሚረዳኝን የመጀመሪያ የሆነውን ደረጃውን የጠበቀ ሞጁል አሰናድቼ ወደ ስራ ልገባ ነው ብሏል፡፡

Comments

00:00