የማስተማር ፍቃዴን ተነጥቄያለሁ ሲል ሌሳንክ ኮሌንስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተናገረ
TRACK

የማስተማር ፍቃዴን ተነጥቄያለሁ ሲል ሌሳንክ ኮሌንስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተናገረ

00:00

ሐምሌ 18፣ 2016

ለ29 ዓመት ተማሪዎችን ሳስተምር የነበረ ቢሆንም፤ በዚህ ሳምንት የማስተማር ፍቃዴን ተነጥቄያለሁ ሲል ሌሳንክ ኮሌንስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተናገረ፡፡

ትምህርት ቤቱን የዘጋው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቢሮ በበኩሉ ትምህርት ቤቱ እስታንዳድር አላሟላም በዚህ ምክንያት ዘግቼዋለሁ ይላል፡፡

ሌሳንክ ኮሌንስ ትምህርት ቤት እስካሁን ሳስተምር የነበረው እስከ 8ኛ ክፍል የነበረ በዚህ ሳምንት ተማሪ ተቀብዬ ለመመዝገብ ፍቃድ ሳድስ ለማስተማር ብቃቱ የለህም ሲል የክፍለ ከተማው ትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እድሳቱን ከልክሎኛል ብሏል፡፡

በዚህ ምክንያት ትምህርት ቤት ውስጥ ሲያስተምሩ የነበሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ለ2017 ማስተማሪያ እያገኘን አይደለም በዚህ ችግር ምክንያት ችግር ውስጥ ነን በማለት ተናግረዋል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ብርሃኑ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በተደጋጋሚ ያሉበት ችግሮች እንዲያስተካክል ቢነገረውም ማረም አልቻለም፡፡

በዚህም ምክንያት ለመዝጋት ተገደናል ይላሉ፡፡

Comments

00:00