00:00
ነሐሴ 15፣2016
ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የሚያገለግል ዘር እጥረት እንዳለባት የግብርና ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍና ሀገሪቱ ያለባት የዘር አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ከግሉ ዘርፍ እስከ መንግስት በጋራ መስራት አለባቸው ቢባልም ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ የዘር ፍላጎቷን በራሷ መሸፈን አልቻለችም፡፡
ይህንን ክፍተት ለመሙላት በሚል ከዚህ አመት ጀምሮ በተከታታይ 3 ዓመታት ኢትዮጵያ በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ኩንታል ዘር ለመሰብሰብ አቅዳ እየሰራች ነው፡፡
ይህ እቅድ በ5 የሰብል ዓይነት የሚያተኩር ሲሆን የሀገሪቱ 87 ከመቶ የምግብ ፍላጎት ይሸፍናሉ፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ብዜት እና ዘር ምርምር ዳይሬክተር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ የዘር አቅርቦት እጥረት በመንግስት አቅም ብቻ አይፈታም ይላሉ፡፡
አሁን የተጀመሩ ስራዎች የሚሳኩት የግሉ ሰርፍ በስፋት ሲሳተፍ ነው ለዚህም በጋራ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
Comments
00:00