ተቆፍረው የተተውና ጉድጓዶች ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነው  መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
TRACK

ተቆፍረው የተተውና ጉድጓዶች ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነው መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

Avatar

ህዳር 16፣2017

ተቆፍረው ክፍት የተተውና ውሃ ያቆሩ ጉድጓዶች ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነው መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ባለፉት የቅዳሜና እሁድ ቀናት በአዲስ አበባ 4 ድንገተኛ አደጋዎች መከሰታቸውን የተናገረው ኮሚሽኑ፤ ከዚህ መካከል አንዱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቡልጋሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለግንባታ በሚል ተቆፍሮ በተተወና ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ እድሜው 20 ዓመት የተገመተ ወጣት ለዋና በሚል ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡

እንዲህ ባለ መልኩ ለግንባታ ተቆፍረው በቸልተኝነት የሚተዉ ጉድጓዶች ተደጋጋሚ አደጋን እያስከተሉ ነው የሚሉት አቶ ንጋቱ ከዚህ ቀደም የሚበዙት በከተማዋ ጫፍ ነበር፤ አሁን ግን በከተማዋ መሃል እየታየ ነው፤ ይህንን አደጋ ያስከተለው ጉድጓድ አሁንም ድረስ ክፍቱን እንደተተወ ነው፤ለግንባታው ፍቃድ የሰጠው አካል ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ እናደርጋለን እስከዚያው ድረስ ግን ቡልጋሪያ አካባቢ ያላችሁ ጠንቀቅ በሉ ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቅዳሜና እሁድ 3 የእሳት አደጋዎች አጋጥመዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሎሜ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ ኢንዱስትሪ መንደር በአንድ ሼድ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ማጋጠሙን እንዲሁም በኮምፌ ቀራኒዮ ሰኔ ሰላሳ ሰፈር በሚባለው አካባቢም በቤቶች ላይ የእሳት አደጋ በሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰና በሸገር ከተማ ቡራዩ ከታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም በ2 መኖሪያ ቤትና ሱቅ ላይ በተነሳው የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ማጋጠሙን ከአቶ ንጋቱ ሰምተናል፡፡

Comments

Avatar