TRACK
የእምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ የማይፈጽሙ፣ ማን ይነካኛል በሚሉ አመራሮች ምክንያት ስራ መስራት አልቻልኩም አለ፡፡
ነሐሴ 22፣2016
የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ የማይፈጽሙ፣ ለህግ የበላይነት የማይገዙ፣ ማን ይነካኛል በሚሉ አመራሮች ምክንያት ስራ መስራት አልቻልኩም አለ፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የሚመሩ አመራሮች «ለምን እነካለው» በሚል የፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ የማይቀበሉ፣ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሰብ የማይፈጽሙ፤ የስራ ኃላፊዎች እንቅፋት እንደሆኑበት ጽህፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡
የእነዚህን አመራሮች መስሪያ ቤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደርግ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡
«የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣውን ህግ አልፈጽም ለህግ የበላይነትም አልገዛም ምን ይነካኛል» ለሚሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዩ ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እና ለክልሉ ምክር ቤት እያሰናዱ እንዳሉም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡
Comments