ሚያዝያ 29 2017
በቴክኒክና ሞያ ተቋማት ውስጥ ክህሎት ያለው የመምህር እጥረት ከፍተኛ መሆኑን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያደረገው ጥናት አሳየ፡፡
በተለይም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በቴክኒክና ሞያ የሚያስተምሩ መምህራን በኢንዱስትሪዎች የመስራት ልምድ ስለሌላቸው በሞያው የክህሎት እጥረት እንደሚታይባቸው ጥናቱ ጠቅሷል፡፡
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ‘’የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ሥርዓት ግንባታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር’’ በሚል ርዕስ ነው ጥናቱን ያደረገው፡፡
በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ የሆኑት እና በዚህ ጥናት ከተሳተፉ ባለሞያዎች መካከል አማረ ማተቡ(ዶ/ር) አንዱ ናቸው፡፡
ከቴክኒክና ሞያ ሰልጥነው የሚወጡ ባለሞያዎች የክህሎት ማነስ እንደሚታይባቸው አምራች ተቋማት ነግረውናል ብለዋል፡፡
Comments