በምስራቅ ሀረርጌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ‘’ሳይበሉ የሚውሉበት ቀን ትንሽ አይደለም’’  ጥናት
TRACK

በምስራቅ ሀረርጌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ‘’ሳይበሉ የሚውሉበት ቀን ትንሽ አይደለም’’ ጥናት

Avatar

ሐምሌ 9፣ 2016

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ማጣት ተደጋግሞ የሚነሳ ችግር ነው፡፡

#በምስራቅ_ሀረርጌ ባሉ ወረዳዎች በሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የተጠና ጥናትም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው፡፡

ጥናቱ በተከናወነባቸው ዘጠኝ ወረዳዎች ያሉ ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳይ ሲነገር ሰምተናል፡፡

‘’የምግብ ዋስትና ማጣት እንደ ሀገር ያለብን ችግር ነው’’ የሚሉት ጥናት አቅራቢዋ ሀና እንዳሻው ‘’በምስራቅ ሀረርጌ የሚታየው ደግሞ ከፍተኛ ነው’’ ብለዋል፡፡

‘’አንድ ሰው የምግብ ዋስትና አለው ወይም የለውም ሊባል የሚችለው በአራት መመዘኛዎች ነው’’ የሚሉት ጥናት አቅራቢዋ ‘’ከነዚህም መካከል በቀን ውስጥ በልቶ ይውላል ወይ የሚለው ቀዳሚው ነው’’ ብለዋል፡፡

Comments

Avatar