ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ደመወዝ ላለመክፈል ሲሉ የተማሩ ሰዎችን እንደማይቀጥሩ ጥናት አሳየ፡፡
TRACK

ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ደመወዝ ላለመክፈል ሲሉ የተማሩ ሰዎችን እንደማይቀጥሩ ጥናት አሳየ፡፡

Avatar

ሚያዝያ 28 2017

ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ደመወዝ ላለመክፈል ሲሉ የተማሩ ሰዎችን እንደማይቀጥሩ ጥናት አሳየ፡፡

በአነስተኛ ደመወዝ የሚቀጥሯቸው በሞያው ያልተማሩ የጉልበት ሰራተኞችም አካባቢውን እስከሚለምዱትና አማራጭ እስኪያገኙ ብቻ የሚቆዩበት በመሆኑ በኢንዱስትሪዎች ብቁ የሰው ሃይል እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት የመኮያ ማህበር አደረግሁት ባለው ጥናት በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ በዩኒቨርሲቲ ለመማር የሚመዘገቡት ቁጥርም ተመናምኗል ብሏል፡፡

አሜሪካ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሃገራት ከሰጠችው ከቀረጥ ነፃ የገበያ እድል ኢትዮጵያ ከተሰረዘች በኋላም የዘርፉ ገበያ መቀዛቀዙን ጥናቱ አሳይቷል ተብሏል፡፡

Comments

Avatar