ታህሳስ 16፣2017
በቤት ሰራኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች መብታቸውን እና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያደርግ ህግ ሊወጣ ነው፡፡
በህጉ መሰረት ከ15 ዓመት በታች የሆኑትን መቅጠር በህግ ያስቀጣል፡፡
በአንድ በኩል የቤት ሰራተኞቹ በአሰሪዎቻቸው ሲበደሉ እና ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እራሳቸው ተቀጣሪዎቹ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ ይስተዋላል፡፡
በአሰሪ እና ሰራተኛ መሀል ያለን ክፍተት ለመድፈንም ይረዳል የተባለ የህግ ማዕቀፍ በቅርቡ ተግበራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ ላይ የቤት ሰራተኞች ባለመካተታቸው በስራ ሂደት ውስጥ ከሚያጋጥሟቸው ወንጀሎች በስተቀር ሌሎች መብቶቻው ሲጣሱ የሚጠይቁበት ህግ እነዳልነበረ ሰምተናል፡፡
Comments