‘’የቤኒሻንጉል ጉሙዝን ከመሀል ሀገር የሚያገናኙ ሁሉም መንገዶች ከ6 ዓመት በፊት ጀምሮ ዝግ ናቸው’’ የምክር ቤት አባል
TRACK

‘’የቤኒሻንጉል ጉሙዝን ከመሀል ሀገር የሚያገናኙ ሁሉም መንገዶች ከ6 ዓመት በፊት ጀምሮ ዝግ ናቸው’’ የምክር ቤት አባል

Avatar

ሚያዝያ 17 2017

የቤኒሻንጉል ጉሙዝን ከመሀል ሀገር የሚያገናኙ ሁሉም መንገዶች ከ6 ዓመት በፊት ጀምሮ ዝግ መሆናቸው፤ አንድ የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አባል ተናገሩ፡፡

የቤኒሻንል ጉሙዝን ከፌዴራል ጋር የሚያገናኙት በነቀምት አሶሳ እና በጎጃም ቻግኒ ያሉት ሁለት መንገዶች መሆናቸውን የጠቀሱት የህዝብ እንደራሴው መንገዶቹ እስካሁን ድረስ ለ6 ዓመታት ዝግ በመሆናቸው ህዝቡ እየተቸገረ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ከክልሉ ወደ መሀል ሀገር መጓጓዣው ብቸኛው መንገድ አውሮፕላን መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም የተነሳ የሸቀጦች፣ መድሃኒት እጥረት እንዲሁም በተለይ አቅም የሌላቸው ሰዎች ለተለያዩ ጉዳዮቻቸው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን እንደራሴው ጠቅሰዋል።

እንደራሴው ይህንን የተናገሩት በትናንትናው እለት በፓርላማው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

Comments

Avatar