የካቲት 10 2017
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ የምግብ ደህንነትን በብቸኝነት የሚቆጣጠር ባለስልጣን እንዲያቋቁሙ ተጠየቁ፡፡
ጥያቄው የቀረበው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብና የስነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር በሆኑት በ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) ነው፡፡
የስነ ምግብ ተመራማሪው በኢትዮጵያ የሚሸጠው፣ የሚለወጠው፣ የሚበላውና የሚጠጣው ምግብ ደህንነቱ ያሳስበኛል፤ ይህንን በብቸንነት የሚቆጣጠር የምግብ ደህንነት ባለስልጣን በአስቸኳይ ይቋቋም ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸውን ነግረውናል፡፡
ላለፉት 20 ዓመታት ለተጠጋ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ ደህንነቱ እየተጠበቀ አይደለም በሚል ጥናቶችንም በማድረግ ከባልደረቦቻቸው ጋር ሲወተውቱ መቆየታቸውን የሚናገሩት ተመራማሪው፤ ለምን በግልዎ ጠየቁ? ለምን በተቋማችሁ አልሆነም? ላልናቸው ችግሩ እየከፋ ቢመጣም እንደተቋም ያለው ውይይት በተበጣጠሰ ደረጃ በመሆኑ በግሌ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ ብለውናል፡፡
ተመራማሪው ዶ/ር አሻግሬ ደብዳቤ ለመፃፍ ያበቋቸው ምክንያቶች፤
Comments