የካቲት 12 2017
መንግስት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ሰዎችን ከመኖሪያም ሆነ ከስራ ቦታቸው ሲያፈናቅል ቀድሞ በደብዳቤ ማሳወቅ፣ ህብረተሰቡንም አነጋግሮ ስለ ጉዳዩ አምነውበት ከቦታው እንዲነሱ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለው የቤት ፈረሳ ግን ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ይህን ሀላፊነት እየተወጡ አይመስልም፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ነዋሪዎች ለሸገር ራዲዮ ያቀረቡት ቅሬታም ይሄንኑ ይመለከታል፡፡
ቅሬታቸውን ሰምተን የወረዳውንም ስራ አስፈፃሚ ጠይቀናል፡፡
Comments