በኢትዮጵያ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ቢዝነስ ምን መሳይ ይሆን?
TRACK

በኢትዮጵያ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ቢዝነስ ምን መሳይ ይሆን?

00:00

ሚያዝያ 6 2017

በኢትዮጵያ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ቢዝነስ ምን መሳይ ይሆን?

በኢትዮጵያ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተፈላጊ እየሆነ ቢመጣም በመንግስት ተገቢው ቁጥጥር ስለማይደረግበት በዘፈቀደ የሚገባበት የስራ መስክ ሆኗል ሲል፤ በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት መካከል የሆነው ምርኩዝ የቤት ለቤት የጤና አገልግሎት የተባለው ድርጅት ተናገረ፡፡

ድርጅቱ ከ4 ዓመት በፊት ሲመሰረት በህክምና ተቋማት ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ቀሪ ህክምናቸውን በቤት ውስጥ እንዲያደርጉ የሚታዘዙ ህሙማንን መንከባከብን ታሳቢ አድርጎ እንደተመሰረተ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛቸው ታምራት ነግረውናል፡፡

Comments

00:00