00:00
ሐምሌ 18፣ 2016
በአዲስ አበባ በተለይ ከቆሻሻ አወጋገድ ጋር ተያይዞ እስከ 100,000 ብር የሚያስቀጣ ደንብ ወጥቷል፡፡
የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱ ባልተሟላበት እንዲህ ያለ ህግ መውጣቱ ምኑ ተያዘና? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡
በከተማዋ ላይ ለሚደረግ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የደረቅም ሆነ የፍሳሽ ቆሻሻን አወጋገድ ጋር ተያይዞ ያለ አግባብ የሚያስወግዱ ግለሰቦች ከ2,000 ብር ጀምሮ እንደሚቀጡ ሰምተናል፡፡
ይሁንና ለማስወገድ የተመቻቸ ነገር በሌለበት ህጉ ተግባራዊ መደረጉ አስጊ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በበኩሉ ሰው ግንዛቤ እንዲኖረው እና ጥንቃቄ እንዲኖረው እንጂ ገንዘብ ለመሰብሰብ አይደለም ሲል ተናግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments
00:00