‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው  ስልጠና ምንነትና ጠቀሜታው ሊፈተሽ እንደሚገባ  የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው
TRACK

‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው ስልጠና ምንነትና ጠቀሜታው ሊፈተሽ እንደሚገባ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው

00:00

ጳጉሜ 1፣2016

‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው ስልጠና ምንነትና ጠቀሜታው ሊፈተሽ እንደሚገባ እና በዚህ ረገድ የቁጥጥር ስርዓት መኖር እንዳለበት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንዶች የስልጠና ማዕከል ከፍተው ሌሎች ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው አነቃቂ በሚል መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ይሰማል፡፡

‘’እኔ በዚህ መንገድ ሄጄ ተሳክቶልኛል፤ እናንተም እንዲሳካላችሁ በዚህ መንገድ ሂዱ’’ ሲሉ መስማት እተለመደ መጥቷል፡፡

በ’’አነቃቂ ንግግር’’ ስም የሚተላለፉ እነዚህና መሰል መልዕክቶች ስርዓት ሊበጅላቸው ይገባል ተብሏል፡፡

‘’አንዳንዶቹ መልዕክቶች በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የካዱ ከመስራት ይልቅ ሰዎችን ወደ ምኞት ዓለም የሚያስገቡ፣በአቋራጭ መንገድ ተጠቅመው የሚፈልጉበት መድረስን የሚያበረታቱ’’ መሆናቸውን እንዳስተዋሉ የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያና አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ አዱኛ ነግረውናል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ አነቃቂዎች ‘’ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት እሳቤ ወጥተው አፈንጋጭ እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ የስኬት መንገድ አነቃቂዎቹ የሚሉት ብቻ እንደሆነ አድርገው የሚያስተምሩ’’ መሆናቸው እንዳሳሰባቸው አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ ያስረዳሉ፡፡

Comments

00:00