በአዲስ አበባ ተጨማሪ 15 የአደጋ ምላሽ መስጫ ጣቢያዎች ሊቋቋሙ መሆኑ ተሰማ፡፡
TRACK

በአዲስ አበባ ተጨማሪ 15 የአደጋ ምላሽ መስጫ ጣቢያዎች ሊቋቋሙ መሆኑ ተሰማ፡፡

00:00

የካቲት 28 2017

በአዲስ አበባ ተጨማሪ 15 የአደጋ ምላሽ መስጫ ጣቢያዎች ሊቋቋሙ መሆኑ ተሰማ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በተለይ በከተማዋ እየተደጋገመ የሚከሰተውን የእሳትና እና መሰል አደጋዎችን በዘላቂነት ለመቀነስ እና በአደጋ ጊዜ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አሁን ካሉት 11 የአደጋ ጊዜ ምላሽ ከሚሰጡ ጣቢያዎች በተጨማሪ 15 ጣቢያዎችን ለማቋቋም እቅድ ይዘናል ብለዋል።

አሁን ላይ የሚስተዋሉ አደጋዎች በ11ዱ ጣቢያዎች ብቻ የሚፈቱ ስላልሆነ ጥናት ባደረግነው መሠረት ከተማዋ 26 የአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚሰጡ ጣቢያዎች ያስፈልጓታል ሲሉ ተናግረዋል።

ለእሳት አደጋ ተጋላጭ የሚሆኑት በተለይ ወንዝ ዳር ተጠጋግተው ባሉ ቤቶች እንደሆነ ያነሱት ስራ አስኪያጁ የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች መከወን ከጀመረ አንስቶ አደጋዎች እዛ አካባቢ ላይ መቀነሱን አስረድተዋል።

አያይዘውም የወንዝ ዳር ልማቶች ለእሳት አደጋ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሐመድ በበኩላቸው በከተማዋ አሁን ላይ የእሳት አደጋዎች እየተደጋገመ የመጣበት ምክንያት በህብረተሰቡ ቸልተኝነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Comments

00:00