በአዲስ አበባ  አንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክፍል እጥረት ስላጋጠማቸው የፈረቃ ትምህርት ለመጀመር እየተገደዱ ነው
TRACK

በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክፍል እጥረት ስላጋጠማቸው የፈረቃ ትምህርት ለመጀመር እየተገደዱ ነው

00:00

ሐምሌ 18፣ 2016

በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ አንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክፍል እጥረት ስላጋጠማቸው የፈረቃ ትምህርት ለመጀመር እየተገደዱ ነው፡፡

ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሁሉም የከተማው የትምህርት ቤት ኃላፊዎችና አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው፡፡

የተለያዩ የክፍለ ከተማ የትምህርት ቢሮ አመራሮች እንደተናገሩት አንዳንድ ወረዳዎች ውስጥ የተማሪ ብዛትና ያለው ክፍል ባለመጣጣሙ በ2017 የትምህርት ዘመን የክፍል ማነስ የገጠማቸው ትምህርት ቤቶች የፈረቃ ትምህርት ለመጀመረ እንደ ወሰኑ ሰምተናል፡፡

በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች በአንድ ክፍል እስከ 90 ተማሪዎች እንደሚማሩ ሲነገር ሰምተናል።

Comments

00:00