00:00
ግንቦት 29፣2016
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያን በሚደረጉ ስብከቶች እና ትምህርቶች ላይ ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ መምህራንና አባቶች እንዳያስተምሩ ከለከለ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በተለይም ግጭትን የሚቀሰቅሱ ስብከቶችን ቤተክርስቲያኗ ከዚህ በኋላ አትታገስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት ሲያካሄደው የነበረው የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን 12 ጉዳዮች ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች በተለመከተ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርትስቲያን ፓትሪያሪክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለተወሱ ውሳኔዎች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ሀገሪቱ ውስጥ ጦርነት እያደረጉ ያሉ አካላት ግጭቶችን በማቆም ችግራቸውን በንግግር ሊፈቱ ይገባል ብለዋል፡፡
Comments
00:00