ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ ህትመት ያሉ ስራዎችን  ጨርሳለች ተባለ
TRACK

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ

Avatar

መስከረም 7 2018

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ።

በጣም ባጠረ ጊዜ ይፋዊ በሆነ ሥነ ሥርዓት የንግድ ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምርም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በመፈረም እና በፓርላማ በማፀደቅ ከቀዳሚዎቹ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ግብይት እንዴት ይፈጸማል? አሰራሩስ በምን የህግ ማዕቀፎች ይመራል የሚሉ እና መሰል ጉዳዮችን የያዘ የትግበራ ስትራቴጂ ማዘጋጀቷ ተነግሯል።

የቀረጥ ሥርዓት የሚመራበት ሰነድም እንዲሁ በገንዘብ ሚኒስቴር መዘጋጀቱን ሠምተናል።

Comments

Avatar