TRACK
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ በሁሉም የመንግስት እና የህብረተሰብ ተቋማት መሬት በመጠቀም ክልሉን የፍራፍሬ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ
00:00
ሐምሌ 17፣ 2016
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ በሁሉም የመንግስት እና የህብረተሰብ ተቋማት መሬት በመጠቀም ክልሉን የፍራፍሬ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ልማት ማዕከል ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ሀላፊው አቶ ኡስማን ሱሩር አዲሱ ክልል ያለው ፀጋ መሬት እና የሰው ሀብት መሆኑን ለሸገር ተናግረዋል፡፡
አንድም መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል መርህ ከቤተሰብ ጊቢ አንስቶ እስከ ማህበረሰብ ተቋማት ድረስ ያለውን ክፍት ቦታ በፍራፍሬ ዛፍ በመሸፈን ከዓመት በኋላ የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ሲሉ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ በጋራ የሚያዘውን ክፍት ቦታ ወይም በአካባቢው አጠራር ጆፎሮ ጭምር በዚህ መንገድ ይሸፈናል ተብሏል፡፡
የጉራጌ ማህበረሰብ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚጠቀምበት የጋራ መሬት ጆፎሮን በፍራፍሬ ዛፍ መሸፈን ምን ጥቅም ያስገኛል? ንብረትነቱስ የማን ይሆናል? ሲል ሸገር ጠይቋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…
የኔነህ ሲሳይ
Comments
00:00