TRACK
የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች በመንግስት ካልተደገፉ የኢትዮጵያን ገበያ በቅርቡ ይቀላቀሉ ከተባሉት የውጭ ሀገራት ነጋዴዎች ጋር መወዳደር እንደሚከብዳቸው ተነገረ
ነሐሴ 21፣2016
የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች በመንግስት ካልተደገፉ የኢትዮጵያን ገበያ በቅርቡ ይቀላቀሉ ከተባሉት የውጭ ሀገራት ነጋዴዎች ጋር መወዳደር እንደሚከብዳቸው ተነገረ።
መንግስት አደረግኩት ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም ከዚህ ቀደም ለውጪ ባለሃብቶች ዝግ ተደርገው የነበሩ እንደ የባንክ እንዲሁም የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ያሉ ዘርፎችን ክፍት እንደሚያደርግ ማሳወቁ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም በሃገር ውስጥ ያሉ ነጋዴዎች በተለያዩ መንገዶች ስጋታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።
በዚህም የሃገር ውስጥ ንግድ ዘርፍ ችግሮችና መፍትሄውን አስመልክቶ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ይኸው ሃሳብ ተነስቷል።
ነጋዴዎቹ እንደሚሉት ቀድሞውንም ቢሆን በቴክኖሎጂም ይሁን በአሰራር ስርዓት ያልዳበረ፣ ለደላሎች የተመቸ የንግድ ሰንሰለት ያለበት በመሆኑና ሌላውም ተዳምሮ ከውጭ ከሚመጡት ጋር መወዳደር ለእኛ ከባድ ነው።
Comments